ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኙን አገደ

በፕሪምየር ሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ እና ረዳቶቹን ከኃላፊነት አግዷል።

ባለፈው ዓመት ቡድኑን ለሁለተኛ ጊዜ ተረክበው ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ የረዱት አሰልጣኝ ግርማ ከክለቡ የእገዳ ደብዳቤ ደርሷቸዋል። ክለቡ በደብዳቤው አሰልጣኙ ለክለቡ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግኖ ቡድኑ በከፍተኛ የውጤት ቀውስ ውስጥ መገኘቱን በመግለፅ ከኃላፊነት ለማገድ መወሰኑን ገልጿል።

ክለቡ ከዋና አሰልጣኙ በተጨማሪ ረዳቱ ኢዘዲን አብደላ እና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙ ምንተስኖት መላኩም አግዷል።

ክለቡ ከእገዳው ውጪ ስለሚኖረው ቀጣይ ሁኔታ ያልገለፀ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ያለውን ሁኔታ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ