ራሱን አግልሎ የነበረው የፋሲል ከነማ ቡድን መሪ ወደ ክለቡ ተመልሷል

የጎንደር ከተማ የበላይ አመራሮች፣ ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የልብ ደጋፊዎች በትናንትናው ዕለት ራሱን ካገለለው ሀብታሙ ዘዋለ ጋር ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዚህም ወደ ቡድኑ ለመመለስ መወሰኑን የክለቡ ታማኝ ምንጮች ገልፀውልናል።

በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፋሲል ከነማ ወልዋሎን ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ እና የክለቡ የጀርባ አጥንት ነው እየተባለ የሚነገርለት ሀብታሙ ዘዋለ ላይ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ራሱን ከክለቡ እንዳገለለ ትናንት አመሻሽ ላይ ዘገበን እንደነበር የሚታወስ ነው።

ክለቡ አመራሮች እንዲሁም የከተማው ከንቲባ ኢንጅነር ማስተዋልን ጨምሮ የክለቡ የልብ ደጋፊዎች ሀብታሙ ዘዋለን አግኝተው በማነጋገር ያለውን ነገር እንደፈቱት እና ሀብታሙ በተፈጠረው ነገር ስሜታዊ ሆኖ እንደወሰነ እና ተቃውሞ ያቀረቡት ደጋፊዎች የክለቡን አቋም እንደማይወክሉ በመግለፅ ተቃውሞ እንኳን ቢኖር አግባብ ባለው መልኩ መሆን እንዳለበት የክለቡ አመራሮች ገልጸዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ