መከላከያን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ያገለገለው ባለሙያ ህይወቱ አለፈ

ከተጫዋችነት እስከ ቴክኒክ ዳይሬክተርነት ያለፉትን ረጅም ዓመታት መከላከያን ያገለገለው ዋስይሁን ማሞ ህይወቱ አልፏል።

በእግርኳስ ተጫዋችነት ዘመኑ ለቀድሞ ምድር ጦር ለአሁኑ መከላከያ ፣ ለኢትዮጵያ መድን እና ሌሎች ክለቦች በተጫዋችነት አገልግሏል። እግር ኳስን ካቆመ በኋላም በመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ለረጅም ዓመታት አገልግሏል። ክለቡ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በነበረው ስኬታማ ቆይታ ትልቅ አስተዋፆኦ ያበረከተው ዋሲሁን ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ትናንት ምሽት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

የቀብር ሥነ-ስርዓቱም ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ለቡ በሚገኘው ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ዛሬ ከቀኑ 09:00 የሚፈፀም ይሆናል።

ሶከር ኢትዮጵያም በዋሲሁን ማሞ ዜና እረፍት የተሰማትን ሀዘን እየገለፀች ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ትመኛለች።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ