ሀዲያ ሆሳዕና ቅጣት ተጣለበት

የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ በሀዲያ ሆሳዕና ላይ ቅጣት መጣሉን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በአስራ ሁለተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና በሜዳው በወልቂጤ ከተማ በተሸነፈበት ጨዋታ በደጋፊው ዘንድ በታየው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ፌዴሬሽኑ ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን በገለልተኛ ሜዳ እንዲያደርግ ቅጣት አሰተላልፏል፡፡

በውሳኔው መሠረት ሀድያ ሆሳዕና በዚህ ሳምንት (በ13ኛው ሳምንት) ወላይታ ድቻን ሲገጥም በቅጣቱ ምክንያት ሀዋሳ ላይ ይጫወታል፡፡ በመቀጠል ደግሞ ጅማ አባ ጅፋርን በዛው ሀዋሳ የ15ኛው ሳምንት ጨዋታውን እንዲያደርግ ኮሚቴው ወስኗል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ