ወልዋሎዎች ቅሬታቸውን ለፌዴሬሽኑ አቀረቡ

ወልዋሎዎች በሜዳ ፍቃድ አሰሳጥ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለዐቢይ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለፁ።

ክለቡ ትናንት በፃፈው ደብዳቤ ቡድኑ የዚህ ሳምንት መርሀ ግብር በሜዳው በወልዋሎ ስታዲየም መጫወት እየተገባው ግልፅ ባልሆነ መንገድ በትግራይ ስታዲየም እንዲካሄድ መወሰኑ እንዳሳዘነው ገፅዋል።

በደብደቤው ከላይ ከተጠቀሰው ቅሬታ ውጭ በዘጠነኛው ሳምንት ላይ ያቀረብኩት ስሞታ መልስ ሳያገኝ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ተቀጥቻለው ያለው ክለቡ አወዳዳሪው አካል የሜዳውን ውሳኔ በድጋሚ እንዲያየው ካልሆነ ደግሞ ክለቡ የራሱን እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ