ስሑል ሽረዎች ወሳኝ ተከላካያቸውን በጉዳት አጥተዋል

የስሑል ሽረው የመሐል ተከላካይ ዮናስ ግርማይ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

ተጫዋቹ ባለፈው ሳምንት ቡድኑ ስሑል ሽረ ሀዋሳ ከተማን ሥስት ለባዶ ባሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ በ56ኛው ደቂቃ በበረከት ተሰማ ተቀይሮ የወጣ ሲሆን ጉዳቱም ከእሁዱ ጨዋታ ውጪ አድርጎታል። እስከ ቀጣይ ሁለት ሳምንታት ድረስ ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችልም ተገምቷል።

ባለፉት ሳምንታት ቡድኑን በአምበልነት የመራው እና በጥሩ ወቅታዊ ብቃት የሚገኘው ይህ ተከላካይ በመጀመርያ ሳምንታት በቅጣት እና በጉዳት ካለፉት ጨዋታዎች ውጭ ቡድኑን በቋሚነት ማገልገሉ ይታወሳል። ከጋናዊው አዳም ማሳላቺ ጋር የሰመረ ጥምረት በመፍጠርም በሊጉ ውስጥ ጥቂት ግቦች ያስተናገደው ጠንካራ የተከላካይ መስመርን በመምራት ጥሩ ግዜ እያሳለፈ ይገኛል።

ከስሑል ሽረ ጋር በተያያዘ ዜና ባሳለፍነው ሳምንት ከውል ጋር በተያያዘ ጨዋታ ያለፈው ዩጋንዳዊው ያሳር ሙገርዋ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል በማራዘሙ ከቡድኑ ጋር ወደ ድሬዳዋ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ