የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ ጀምረው ሲከናወኑ የመርሐ ግብሩ አካል የሆኑ አራት ጨዋታዎች የቀን ለውጥ ተደርጎባቸዋል።
ለውጥ ከተደረገባቸው ጨዋታዎች መካከል የሀዲያ ሆሳዕና እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ አንዱ ነው። ጨዋታው እሁድ አቢዮ ኤርሳሞ ላይ እንዲከናወን ቢወሰንም ሀዲያ ሆሳዕና ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን በገለልተኛ ሜዳ እንዲያደርግ በመቀጣቱ ምክንያት ወደ ሀዋሳ ተዘዋውሯል። በዚህም ማክሰኞ የካቲት 3 የሚከናወን ይሆናል።
በሀዋሳ ቅዳሜ እና እሁድ ሊደረጉ የነበሩት ሁለት ጨዋታዎች በአንድ ቀን ተገፍተው እሁድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ቅዳሜ የነበረው የሀዋሳ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ እሁድ ሲወናወን እሁድ የነበረው የሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ ጨዋታ ወደ ሰኞ ተሸጋሽጓል። የእነዚህ ጨዋታዎች የቀን መሸጋሸግ ምክንያት ግን አልታወቀም።
ሌላው በዚህ ሳምንት የቀን ሽግሽግ የተደረገበት ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታ ነው። እሁድ ሊደረግ የነበረው ይህ መርሐ ግብር በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ምክንያት ወደ ሐሙስ የካቲት 5 (10:00) ሊሸጋገር ችሏል።
የተሻሻለው የ13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይህንን ይመስላል
13ኛ ሳምንት | ||
ቅዳሜ ጥር 30 ቀን 2012 | ||
መቐለ 70 እንደርታ | 9:00 | ፋሲል ከነማ |
እሁድ የካቲት 1 ቀን 2012 | ||
ሀዋሳ ከተማ | 9:00 | ጅማ አባ ጅፋር |
ባህር ዳር ከተማ | 9:00 | ሰበታ ከተማ |
ድሬዳዋ ከተማ | 9:00 | ስሑል ሽረ |
ወልዋሎ ዓ/ዩ | 9:00 | ቅዱስ ጊዮርጊስ |
ሰኞ የካቲት 2 ቀን 2012 | ||
ሲዳማ ቡና | 9:00 | አዳማ ከተማ |
ማክሰኞ የካቲት 3 ቀን 2012 | ||
ሀዲያ ሆሳዕና | 9:00 | ወላይታ ድቻ |
ሐሙስ የካቲት 5 ቀን 2012 | ||
ኢትዮጵያ ቡና | 10:00 | ወልቂጤ ከተማ |
©ሶከር ኢትዮጵያ