ደደቢት ከ ሀዋሳ ከተማ : ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ደደቢት 3-0 ሀዋሳ ከተማ

45’ዳንኤል ደርቤ (በራሱ ላይ)
58′ 86′ ዳዊት ፍቃዱ

———*——–

ተጠናቀቀ : ደደቢት 3-0 ሀዋሳ ከተማ

* ሀዋሳ ከተማ ወደፊት ለመሄድ ፍላጎት የማይታይበት እና የተዳከመ እንቅስቃሴ አሳይቶ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡

4ኛ ዳኛው 3 ተጨማሪ ደቂቃዎች ጨምረዋል፡፡

88′ ሁለት ግብ ያስቆጠረው ዳዊት ፍቃዱ በወግደረስ ታዬ ተቀይሮ ወጥቷል፡፡

* ሳኑሚ ከሳምሶን የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ወደ ግብ የላከው ኳስ የግቡ ቋሚ ሲመልሰው ዳዊት አግኝቷት ወደ ግብነት ቀይሯታል፡፡

86′ ጎል!!! ዳዊት ፍቃዱ

80′ የተጫዋች ቅያሪ : ደደቢት
ኄኖክ ካሳሁን በያሬድ ዝናቡ ተቀይሮ ገብቷል::

71′ ስዩም ተስፋዬ ከቀኝ መስመር ያጠፈለትን ንፁህ የግብ ማግባት እድል ዳዊት ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

65′ የተጫዋች ቅያሪ – ደደቢት
አለምአንተ ካሳሁን ኄኖክ ኢሳያስን ቀይሮ ገብቷል፡፡

63′ የተጫዋች ቅያሪ : ሀዋሳ ከተማ
መስቀሌ መንግስቱ ገብረሚካኤል ያዕቆብን ቀይሮ ገብቷል፡፡

*ዳዊት ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አርፏል፡፡

58′ ጎል!!!! ዳዊት ፍቃዱ

55′ የተጫዋች ቅያሪ – ሀዋሳ ከተማ
ዮሃንስ ሌጌቦ እና እስራኤል እሸቱ ገብተው ኤፍሬም ዘካርያስ እና ፍርዳወቅ ሲሳይ ወጥተዋል፡፡

48′ ታፈሰ ሰለሞን በግምት ከ25 ሜትር የመታት ኳስ ኢላማዋን ስታ ወደ ውጪ ወጥታለች፡፡

46′ ያሬድ ዝናቡ ያሻማውን ኳስ ሳኑሚ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

2ኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ከመልበሻ ክፍል ወጥተዋል፡፡ 2ኛው አጋማሽ ሊጀመር ጥቂት ደቂቃ ቀርቶታል፡፡

************//************

እረፍት : የመጀመርያው አጋማሽ በደደቢት 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

*ሀዋሳ ግቡ ከመቆጠሩ በፊት የደደቢት ተጫዋቾች ጥፋት ሰርተዋል በሚል ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡ ክስም አስመዝግበዋል፡፡

ጎል!! ዳንኤል ደርቤ በራሱ ግብ ላይ
አስቆጥሯል፡፡

42′ ጋዲሳ መብራቴ ከቀኝ መስመር ወደ ግብ የሞከረውን ኳስ ታሪክ ጌትነት በቀላሉ ይዞበታል፡፡

37′ ጨዋታው በሃዋሳ የግብ ክልል እየተደረገ ነው፡፡ ደደቢቶች ጫና መፍጠር ቢችልም የግብ እድል መፍጠር አልቻለም፡፡

35′ ስዩም ተስፋዬ ከቀኝ መስመር ወደ ግብ የላካት ኳስ በዮሃንስ በዛብህ ተመልሳበታለች

26′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው፡፡ ሳኑሚ በርቀት የሚጣልለትን ኳስ ከተከላካዮች ጀርባ በፍጥነት በመገኘት ለመጠቀም እየሞከረ ይገኛል፡፡ ሀዋሳ ደግሞ በተደራጀ ሁኔታ ወደ ፊት ለመሄድ በመሞከር ከደደቢት ተሽለዋል፡፡

12′ ሽመክት ጉግሳ በሀዋሳ ተከላካዮች አናት ከፍ አድርጎ ያሻገረለትኅ ኳስ ሳኑሚ በፍጥነት አግኝቶ ወደ ግብ ቢሞክርም ዮሃንስ ወደ ውጪ አውጥቶበታል፡፡

5′ ሁለቱም ቡድኖች አንድ አንድ ኳስ ሞክረዋል፡፡ በተለይ የሳሙኤል ሳኑሚ ሙከራ አስደንጋጭ ነበር፡፡

ጨዋታው ተጀመረ ፡ ደደቢት 0-0 ሀዋሳ ከተማ
– – – – – –
የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ
ዮሃንስ በዛብህ
ዳንኤል ደርቤ – ሙጂብ ቃሲም – ግርማ በቀለ – ደስታ ዮሃንስ
ሙሉጌታ ምህረት – ኤፍሬም ዘካርያስ – ታፈሰ ሰለሞን
ገብረሚካኤል ያዕቆብ – ፍርዳወቅ ሲሳይ – ጋዲሳ መብራቴ

——–

የደደቢት አሰላለፍ
ታሪክ ጌትነት
ስዩም ተስፋዬ – አይናለም ኃይለ – አክሊሉ አየነው – ተካልኝ ደጀኔ
ሽመክት ጉግሳ – ያሬድ ዝናቡ – ሳምሶን ጥላሁን – ኄኖክ ኢሳይያስ
ሳሚ ሳኑሚ – ዳዊት ፍቃዱ
——-
ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል ገብተዋል

ያጋሩ