የወልዋሎ እና የአሰልጣኝ ዮሐንስ ጉዳይ

👉”መረጃው ከእውነት የራቀ ነው” የቡድን መሪ አቶ ሀዲ ሰዊ እና የቦርድ አባል አቶ ይትባረክ ሥዩም

👉” ቦርዱ አሰልጣኙ እንዲሰናበት ወስኗል” አሸናፊ አማረ (የቡድኑ ስራ አስከያጅ)

ከደቃቃዎች በፊት ሶከር ኢትዮጵያ ከወልዋሎ ሥራ አስከያጅ አቶ አሸናፊ አማረ ባገኘችው መረጃ የቡድኑ የአመራር ቦርድ አሰልጣኙን ለማሰናበት መወሱን መግለጿ ይታወሳል። ሆኖም የተቀረው የቡድኑ አመራሮች በዋነኝነት የቡድን መሪው አቶ ሀዲ ሰዊ መረጃው ከእውነት የራቀ እንደሆነ ገልፀዋል። “የቦርድ አመራሩ ጭራሽ አልተሰበሰበም ፤ መረጃው ከየት እንደመጣ አላውቅም።” ብለዋል። ክለቡ የቦርድ አባል አቶ ይትባረክም ከቡድን መሪው ጋር ተመሳሳይ ሀሳባቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ከተቀሩት የቦርዱ አባላት ካገኘኘነው መረጃ በኋላ መረጃውን የሰጡንን ሥራ አስከያጁ አቶ አሸናፊ አማረን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ሥራ አስከያጁ ስልኩ ባለማንሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።

በጉዳዩ ዙርያ ያሉትን ተጨማሪ መረጃዎች ተከታትለን እናቀርባለን።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ