የሦስት ተጫዋቾች የሙከራ ጉዞ ተጨናገፈ

ወደ መቄዶንያ የሙከራ ዕድል አግኝተው የነበሩ ሦስት ተጫዋቾች ሊያደርጉት የነበረው የሙከራ ጉዞ ተሰናክሏል።

ወደ መቅዶንያ የሙከራ ዕድል አግኝተው የነበሩት ተጫዋቾች የመቐለ 70 እንደርታው ተከላካይ አሌክስ ተሰማ፣ የባህርዳር ከተማው አማካይ ፍፁም ዓለሙ እና የድሬዳዋ ከተማው ያሬድ ዘውድነህ ሲሆኑ የእክሉ ምክንያት የዝውውር መስኮቱ በመዘጋቱ መሆኑ ታውቋል።

የመቅዶንያው ክለብ ሲሌክስ ቀደም ብሎ ለተጫዋቾቹ የሙከራ ግብዣ ወረቀት ልኮ የነበረ ቢሆንም የጉዞ ሒደቱ በመጓተቱ ምክንያት ወደ ስፍራው ሳያቀኑ የጥር የዝውውር መስኮት እንደተዘጋ ሰምተናል።

ተጫዋቾቹ በዚህ ወቅት ጉዟቸው ባይሳካም የሙከራ ጊዜው ወደ ቀጣዩ የክረምት የዝውውር መስኮት ሊዘዋወርላቸው የሚችልበት ዕድል የሰፋ መሆኑ ተገልጿል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ