በቀጣይ ሳምንታት የሚደረጉ አራት ጨዋታዎች ላይ ሽግሽግ ተደርጓል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 14ኛ እና 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲደረጉ አራት ጨዋታዎች ሽግሽግ ተደርጎባቸዋል።

14ኛ ሳምንት

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔን ተከትሎ ወደ ሐሙስ በተሸጋገረው የኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታ (13ኛ ሳምንት) ምክንያት ሁለቱ ቡድኖች በ14ኛ ሳምንት የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ወደ ሰኞ ተሸጋግሮላቸዋል። በዚህም መሠረት ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ሰኞ የካቲት 9 አአ ስታዲየም ላይ በ10:00 የሚጫወቱ ሲሆን ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና ወልቂጤ ላይ በተመሳሳይ ሰኞ የካቲት 9 ወልቂጤ ላይ ይጫወታሉ።

የ14ኛ ሳምንት ሙሉ መርሐ ግብር

ቅዳሜ የካቲት 7

9:00 መቐለ 70 እንደርታ ከ ሀዋሳ ከተማ

እሁድ የካቲት 8

9:00 ጅማ አባ ጅፋር ከ ድሬዳዋ ከተማ
9:00 ስሑል ሽረ ከ ሀዲያ ሆሳዕና
9:00 አዳማ ከተማ ከ ወልዋሎ
9:00 ወላይታ ድቻ ከ ባህር ዳር ከተማ
9:00 ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሰኞ የካቲት 9

9:00 ወልቂጤ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና
10:00 ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

15ኛ ሳምንት

በዚህም ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ላይ ሽግሽግ ተደርጓል። በዚህም መሠረት ሁለተኛ የሜዳ ቅጣቱን ተግባራዊ የሚያደርገው ሀዲያ ሆሳዕና ከጅማ አባ ጅፋር የሚያደርገው ጨዋታ ሀዋሳ ላይ ዓርብ የካቲት 13 ሲደረግ ሲዳማ ቡና ከሰበታ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ቅዳሜ የካቲት 14 የሚከናወን ይሆናል።

የ15ኛ ሳምንት ሙሉ መርሐ ግብር

ዓርብ የካቲት 13

9:00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ ጅማ አባ ጅፋር (ሀዋሳ)

ቅዳሜ የካቲት 14

9:00 ሲዳማ ቡና ከ ሰበታ ከተማ
9:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ

እሁድ የካቲት 15

9:00 ወልዋሎ ከ ወልቂጤ ከተማ (ዓዲግራት)
9:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ
9:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ
9:00 ባህር ዳር ከተማ ከ ስሑል ሽረ
9:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ መቐለ 70 እንደርታ

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ