የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኢያሱ መርሐ ፅድቅ ያቀረቡትን የሥራ መልቀቂያ መቀበሉን አስታውቋል።
ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀኃፊ ሆነው የተሾሙት ኢያሱ መርሐ ፅድቅ (ዶ/ር) ከሥራቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን የገለፀው ፌዴሬሽኑ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ከትናንት የካቲት 4 ቀን 2012 ጀምሮ ከፌዴሬሽኑ ጋር መለያየታቸውን በድረ-ገፁ አስታውቋል።
እንደ ፌዴሬሽኑ ገለፃ ግለሰቡን በመተካት የህዝበረ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን በጊዜያዊነት ቦታውን የሚሸፍኑ ይሆናል።
የፌዴሬሽኑ ዋና ፀኃፊነት ቦታ ባለፉት ዓመታት መረጋጋት ከማይታይባቸው ቦታዎች አንዱ ሲሆን ባለፉት 5 ዓመታት አምስት ግለሰቦች በቋሚ እና በጊዜያዊነት ሰርተዋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ