ወልዋሎ ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር መለያየቱ እርግጥ ሆኗል

ላለፈው አንድ ዓመት ከወልዋሎ ጋር ቆይታ የነበራቸው አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሎ ለቡድናቸው ያቀረቡት የልቀቁኝ ደብዳቤ በክለቡ ተቀባይነት አግኝቷል።

ከክለቡ እንዳገኘነው መረጃ ቡድኑ በቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች በምክትል አሰልጣኞቹ አብርሀ ተዓረ እና ኮማንደር ኪዳነ ሀፍተ እየተመራ ጨዋታዎች እንደሚያደርግ እና በቀጣይ ቀናትም አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴ እንደሚጀምር ታውቋል።

ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ይትባረክ ሥዩምም አሰልጣኙ በጋራ ስምምነት ከቡድኑ ጋር እንደተለያዩ ገልፀው ክለቡ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር በቅርቡ እንቅስቃሴ እንደሚጀምር ገልፀዋል። “አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ያቀረቡት የመልቀቅያ ደብዳቤን ክለቡ ተቀብሎታል። ቡድናችን ቀጣይ ጨዋታዎች በምክትል አሰልጣኞች እየተመራ ጨዋታ ያደርጋል፤ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ጉዳይም በቅርቡ እንቅስቃሴ ይጀመራል።” ብለዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ