ፕሪሚየር ሊግ ፡ ደደቢት እና ድሬዳዋ ድል ቀንቷቸዋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ 2 ጨዋታዎች ሲጀምር ደደቢት እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በ9፡00 አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ኤሌክትሪክን የገጠመው ድሬዳዋ ከተማ 1-0 በማሸነፍ ደረጃውን ከፍ አድርጓል፡፡ በ58ኛው ደቂቃ የድሬዳዋ ከተማን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው ፍቃዱ ታደሰ ነው፡፡ ድሬዳዋ ከተማዎች ወደ ግብ በመድረስ ፣ የግብ ሙከራ በማድረግ እና በኳስ ቁጥጥር ከኤሌክትሪክ የተሸሉ ሆነው ታይተዋል፡፡

ድሉን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ ደረጃውን ወደ 4ኛ ሲያሳድግ ኤሌክትሪክ አንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ 9ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል፡፡

በ11፡30 ደደቢት በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ በቀላሉ 3-0 አሸንፏል፡፡ የደደቢት ቀዳሚ ግብ የተገኘችው የመጀመርያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 1 ደቂቃ ሲቀረው ሲሆን ዳንኤል ደርቤ በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡ ሀዋሳዎች ግቧ ከመቆጠሯ በፊት የደደቢት ተጫዋቾች ጥፋት ሰርተዋል በሚል ክስ አስመዝግበዋል፡፡

ከእረፍት መልስ ይበልጥ ተጭነኖ የተጫወተው ደደቢት በ58ኛው እና 86ኛው ደቂቃ በዳዊት ፍቃዱ አማካኝት ተጨማሪ ግቦች ማስቆጠር ችሏል፡፡ ዳዊት ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጪ አክርሮ በመምታት ያስቆጠራት የጨዋታው ሁለተኛ ግብ ድንቅ ነበረች፡፡

ድሉ ደደቢት ነጥቡን ወደ 18 አሳድጎ መሪዎቹን እንዲጠጋ ሲያስደርግ ሀዋሳ በ9 ነጥብ ወራጅ ቀጠናው ላይ እንዲቆይ አድርጎታል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላሉ፡፡

የጨዋታዎቹ ፕሮግራም ይህንን ይመስላል፡-

new 222

የደረጃ ሰንጠረዥ፡-

new 333333

የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ፡-

new 1

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *