አስተያየት  | አዳማ ከተማ 2-0 ወልዋሎ ዓ/ዩ

ከዛሬ ጨዋታዎች መካከል አዳማ ከተማ ወልዋሎን 2-0 ካሸነፈ በኋላ የአዳማው ምክትል አሰልጣኝ ደጉ ዱባም ተከታዩን አስተያየት የሰጡ ሲሆን በወልዋሎ በኩል ግን የአሰልጣኝ ቡድን አባላቱ በቶሎ ሜዳ ለቀው በመውጣታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።


“ጨዋታው ከመጀመሪያው ጀምሮ ለማጥቃት የተጫወትንበት ነበር” የአዳማ ምክትል አሰልጣኝ ደጉ ዱባም

ስለጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለማጥቃት የተጫወትንበት ነበር። ያደረግነው እንቅስቃሴም ጥሩ ነበር ውጤቱም መልካም ሆኖልናል።


ስለፉአድ ያለቦታው መሰለፍ እና በጊዜ መቀየር

በመጀመሪያ በሦስት ተከላካይ አድርገን ፉዓድ ያለቦታው ቢሆንም እየሄደ እንዲያጠቃ ነበር ያሰብነው። የለወጥነውም በታክቲካዊ ምክንያት እንጂ ጥሩ ሳይሆን ቀርቶ አልነበረም። እውነተኛ የመስመር ተከላካይ ለመጠቀም በማሰብ ነበር ለውጡን ያደረግነው።


ስለተጨዋቾች የደሞዝ ጥያቂ ወቅታዊ ሁኔታ

አሁን ጥሩ ነው  ፤ መስመር ይዟል። ለዛም ነው በዚህ ሳምንት መደበኛ ልምምዳችንን ስናደርግ የቆየነው። ከአመራሩም ጥሩ ነገር ስላለ እንደሚስተካከል እርግጠኛ ነኝ። ያም ስለሆነ ነው ተጨዋቾቹም ተነሳሽነታቸው ጥሩ የሆነው ፤ የሚቀጥለው ሳምንት ላይ ደግሞ ሁሉ ነገር እንደሚያልቅ ቃል ተገብቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ