ፈረሰኞቹ ወሳኝ ተጫዋቻቸውን በጉዳት ያጣሉ

በዘንድሮ የውድድር ዓመት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ጥሩ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ጋዲሳ መብራቴ ጉዳት አስተናግዷል።

በ14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጎንደር ፋሲለደስ ስታድየም የተካሄደው የዐፄዎቹ እና የፈረሰኞቹ ተጠባቂ ጨዋታ በሁለት አቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወቃል። በጨዋታው እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት አስተናግዶ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው እና ክለቡን አንድ አቻ ያደረገውን ጎል በግሩም ሁኔታ ያስቆጠው ጋዲሳ መብራቴ ትከሻው ላይ ከበድ ያለ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ሊወጣ ችሏል።

ለተሻለ ህክምና ወደ ጎንደር አጠቃላይ ሆስፒታል ያመራው ጋዲሳ ትከሻው ላይ ስብራት እንዳጋጠመው የተረጋገጠ ሲሆን በቀጣይ የኤክስሬይ ውጤቱ ታይቶ ተጫዋቹ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚያርቀው እንደሚታወቅ ለማወቅ ችለናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ