የወልዋሎ የመጀመርያው ተሰናባች ተጫዋች ታውቋል

ኬነዲ አሽያ ከቡድኑ ጋር እንደተለያየ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

ጋናዊው አማካይ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወልዋሎን ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም እንደተጠበቀው ቡድኑን ያላገለገለ ሲሆን በቆይታው 3 ጨዋታዎች ላይ ተቀይሮ በመግባት 71 ደቂቃዎች ብቻ ተጫውቶ ተሰናብቷል። ይህ ተጫዋች ከ2 ዓመታት በፊትም በተመሳሳይ በሲዳማ ቡና ቆይታው ቡድኑን ሳያገለግል መሰናበቱ ይታወሳል።

በሁለተኛው ዙር በአዲስ አሰልጣኝ ይቀርባሉ ተብለው የሚጠበቁት ወልዋሎዎች በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾች ሊያሰናብቱ እንደሚችሉ ታውቋል።

በሌላ ከቡድኑ ጋር የተያያዘ ዜና ከአስራ ዘጠኝ ወራት የመቐለ ቆይታ በኃላ ወደ ዓዲግራት የተመለሱት ወልዋሎዎች በደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ