ልማደኛዋ ሎዛ የሊግ ጎሎቿን ብዛት 30 አደረሰች

የማልታ ፕሪምየር ሊግ መሪ የሆኑት ቢርኪርካራዎች ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ራይደርስን 10-2 ሲያሸንፉ ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ አራት ግቦች አስቆጥራ በሊጉ ያስቆጠረቻቸው ግቦችን ቁጥር ሰላሳ አድርሳለች።

ሊያልቅ የአምስት ጨዋታ ዕድሜ ብቻ የቀረው የማልታ ሊግ ቢርኪርካራዎች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ካሉት ማግር በስድስት ነጥብ ርቀው ሲገኙ ሎዛ አበራም በመጀመርያው ዓመት የማልታ ቆይታዋ ቡድኑ ኳስቆጠረው ሰባ ስድስት ግብ ሰላሳው አስቆጥራ የግብ አነፍናፊ መሆኗን አስመስክራለች።

በቀጣይ ኪርኮፕን የሚገጥሙት ቢርኪርካራዎች ይህን የሊግ ዋንጫ የሚያነሱ ከሆነ በቀጣይ ዓመት በአውሮፓ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ መሳተፋቸውን ያረጋግጣሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ