የፕሪምየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ቁጥሮች እና እውነታዎች

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 14ኛ ሳምንትን የተመለከቱ ቁጥራዊ መረጃዎች እና እውነታዎችን በሚከተለው መልኩ አሰናድተናል።

👉 ጎሎች በቁጥራዊ መረጃ

– በአስራ ሦስተኛው ሳምንት 17 ጎሎች ተቆጥረዋል። ይህም ባለፈው ሳምንት ከተቆጠረው የጎል ብዛት በ6 ዝቅ ያለ ነው።

– ባለፉት ሳምንታት በየጨዋታው ጎል ሲቆጠርበት የነበረው ሊግ በዚህ ሳምንት ግን ሁለት ጨዋታዎች (ሽረ/ሆሳዕና እና ሰበታ/ቡና) ጎል ሳይቆጠርባቸው ተጠናቀዋል።

– በዚህ ሳምንት ጎል ሳያስቆጥሩ የወጡ ቡድኖች ካላፈው ሳምንት በአራት ከፍ ብሎ 7 ሆኗል። ሆሳዕና፣ ሽረ፣ ባህር ዳር፣ ቡና፣ ሰበታ፣ ወልቂጤ እና ወልዋሎ ያላስቆጠሩ ቡድኖች ናቸው።

– በዚህ ሳምንት 15 ተጫዋቾች ጎል በማስቆጠር ተሳትፈዋል። ኦኪኪ አፎላቢ ሦስት ጎሎች በማስቆጠር ቀዳሚውን ቦታ ሲይዝ ቀሪዎቹ 14 ተጫዋቾች አንድ አንድ ጎሎች አስቆጥረዋል።

– ከተቆጠሩት 17 ጎሎች መካከል 13 ጎሎች በአጥቂ (የመሐል እና የመስመር) ተጫዋቾች ሲቆጠሩ 2 ጎሎች በአማካይ ሥፍራ ተጫዋቾች፤ በተመሳሳይ 2 ጎሎች በተከላካዮች ተቆጥረዋል።

– ከ17 ጎሎች መካከል 13 ጎሎች ከክፍት ጨዋታ ሲቆጠሩ አንድ በቀጥታ ቅጣት ምት፣ 3 ጎሎች ደግሞ በፍፁም ቅጣት ምት ተቆጥረዋል።

– ከ17 ጎሎች መካከል 15 ጎሎች ሳጥን ውስጥ ተመትተው ሲቆጠሩ 2 ጎሎች ከሳጥን ውጪ ተመትተው ጎል ሆነዋል።

👉 ካርዶች በዚህ ሳምንት

– በዚህ ሳምንት 39 የማስጠንቀቂያ እና 4 የቀይ ካርዶች ተመዘውበታል። ይህም በቢጫም ሆነ በቀይ ካርድ ቁጥር የዘንድሮው ሊግ ከተጀመረ ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

– አዳማ ከተማ (0) ከወልዋሎ (2) ያደረጉት ጨዋታ በሁለት የማስጠንቀቂያ ካርዶች ዝቅተኛው ሆኖ ሲመዘገብ ሰበታ ከተማ (5) ከ ኢትዮጵያ ቡና (6) ደግሞ በ11 የማስጠንቀቂያ ካርድ ከፍተኛው ነው። ፋሲል ከነማ (1) ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (1) ሁለት ቀይ ካርድ የተመዘዘበት ሆኖም አልፏል።

– የዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ ፈጣኑ ቀይ ካርድ በጅማ እና ድሬዳዋ መካከል በተደረገው ጨዋታ ላይ ተመዝግቧል። የጅማው አሌክስ አሙዙ በ8ኛው ደቂቃ…

– አዳማ ከተማ በዚህ ሳምንት ምንም የማስጠንቀቂያ ካርድ ያልተመለከተ ቡድን ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በ6 ከፍተኛው ነው።

👉 በዚህ ሳምንት…

– በዚህ ሳምንት ስድስት ተጫዋቾች ዘንድሮ በሊጉ ለመጀመርያ ጊዜ ጎል አስቆጥረዋል። አዙካ ኢዙ (ፋሲል)፣ አማኑኤል ጎበና (አዳማ ከተማ)፣ ተመስገን ደረሰ ( ጅማ አባ ጅፋር)፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ እና ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ (መቐለ 70 እንደርታ) እንዲሁም በረከት ሳሙኤል (ድሬዳዋ) ለመጀመርያ ጊዜ ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

👉 የኦኪኪ ሐት-ትሪክ 

በዚህ ሳምንት ብቸኛው ከአንድ ጎል በላይ ያስቆጠረው ተጫዋች ኦኪኪ ነው። ለመቐለ የመጀመርያ ሐት-ትሪኩን የሰራው ኦኪኪ አፎላቢ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሦስተኛ ሐት-ትሪኩ ሆኖ የተመዘገበለት ሲሆን በ2010 የመጨረሻ ሳምንት አዳማ ላይ አራት ጎል ካስቆጠረ በኋላ የተገኘ ነው። 



© ሶከር ኢትዮጵያ

በሶከር ኢትዮጵያ የሚወጡትን ቁጥራዊ መረጃዎች እና እውነታዎች በቀጥታም ሆነ በግብዓትነት ሲጠቀሙ ምንጭ ይጥቀሱ።