የሊጉ ክለቦች የሚመሰገኑበት መድረክ ሊዘጋጅ ነው

ሊጉን የማወዳደር ስልጣን ለዐቢይ ኮሚቴ የሰጠው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሊጉ እስካሁን ባለው ጉዞ በአንፃራዊ ሰላም መካሄዱን ተከትሎ ተሳታፊ ቡድኖችን እና ደጋፊዎቻቸውን ሊያመሰግን ነው።

ባለፉት ዓመታት በርካታ የደጋፊዎች ስርዓት አልበኝነት የታየበት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዘንድሮ በብዙ መልክ ተሻሽሎ ጨዋታዎች በአንፃዊነት በሰላም እየተጠናቀቁ ይገኛሉ። ፌደሬሽኑ፣ የሊግ ኮሚቴው እንዲሁም የስፖርት ኮሚሽን እና የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ይህን የክለቦች እና ደጋፊዎች መልካም ተግባር ዕውቅና ለመስጠት የምስጋና መድረክ ለማዘጋጀት ቅድም ዝግጅቱ ተጠናቋል። የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 21 በሸራተን አዲስ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ የሚጀምርም ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ