በቅድመ ውድድር ላይ ጉዳት አጋጥሞት ላለፉት ስድስት ወራት በጉዳት ላይ የቆየው የመቐለው አምበል ሚካኤል ደስታ ህክምናው አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።
ከባድ የጉልበት ጉዳት አስተናግዶ ለህክምና ወደ ጣልያን ያመራው አማካዩ ህክምናው በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ በጥሩ ጤንነት ሲገኝ መቐለ ሀዋሳን ሲያሸንፍ ከበርካታ ጊዜያት በኃላ በስታዲየም ተገኝቶ ጨዋታውን ተከታትሏል። አማካዩ በቀጣይ ሳምንታት በግሉ የሜዳ ልምምድ ጀምሮ በሁለተኛው ዙር ቡድኑን ለማገልገል በዝግጅት ሲገኝ ተጫዋቹ ከጉዳት መመለሱም በአማካይ ተጫዋቾች አማራጭ ለተቸገሩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ጥሩ ዜና ነው።
በ2010 መከላከያን ለቆ መቐለ ከተቀላቀለ በኃላ ላለፉትን ዓመታት ቡድኑን በአምበልነት የመራው አንጋፋው አማካይ በሜዳ ውስጥ ከሚሰጥው አገልግሎት በተጨማሪ ሁለተኛ ተከታታይ የሊግ ክብር ለሚያልሙት ምዓም አናብስት በልምድ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሎለታል።
© ሶከር ኢትዮጵያ