አርባምንጭ ከተማ ከ ዳሽን ቢራ ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አርባምንጭ ከተማ 0-0 ዳሽን ቢራ
———–//———–

ተጠናቀቀ!!!
የጨዋታው ካለግብ ተጠናቋል፡፡

* በጨዋታው ፀጋዬ አበራ ከአርባምንጭ ፣ ደረጄ መንግስቴ ከዳሽን ቢጫ ካርድ ተመልክተዋል፡፡

image-0978e09df58a0d70daff81b703c8f9a12c5de53de15444794d3e299d2f01d929-V

73′ ከማዕዘን የተመታ ኳስ በእጅ ቢነካም ዳኛው ፍፁም ቅጣት ምት ከልክለዋል በሚል የዳሽን ተጫዋቾች ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

70′ ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር እየተደረገበት ነው፡፡ በ65ኛው ደቂቃ ተሾመ ታደሰ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝቶ በግብ ጠባቂው ተመልሶበታል፡፡

63′ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኤዶም ሆውሶሮቪ ወደ ግብ ሞክሮ ግብ ጠባቂው መልሶበታል፡፡

55′ ዳሽን ቢራዎች ከመጀመርያው አጋማሽ በተለየ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ በኤዶም ሆውሶሮቪ አማካኝነትም ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

******/*******

የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡

37′ ታደለ መንገሻ የመታው ቅጣት ምት የብረቱ አግዳሚ መልሶበታል፡፡

32′ የአርባምንጭ ተጫዋቾች አንድ ሁለት ተቀባብለው በታደለ መንገሻ አማካኝነት ወደ ግብ የሞከሩት ኳስ ወደውጪ ወጥቷል፡፡

26′ አምሳሉ ጥላሁን የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቶበታል፡፡

20’ጨዋታው በአርባምንጭ የበላይነት የቀጠለ ሲሆን ግብ ለማግኘት በአጥቂዎቹ አማካኝነት ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡

image-6a6e602fbf4ab086fa9d454d04d128d8a15257b2fbdce9e27dc9a11d95e96136-V

10′ አርባምንጭ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ በረከት እና ተሾመ ለግብ የቀረበ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ዳሽኖች በራሳቸው ሜዳ የተገደበ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡

1′ ጨዋታው ተጀመረ:: ዳሽን ከቀኝ ወደ ግራ ሲያጠቃ አርባምንጭ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃል፡፡
———-
ሁለቱም ቡድኖች ከመልበሻ ክፍል ወጥተው ሰላምታ እየተሰጣጡ ነው፡፡
———

ሁለቱም ክለቦች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

* በረከት ቦጋለ ፣ በረከት ወልደፃዲቅ እና ተሾመ ታደሰ ከጉዳት እና ግል ጉዳይ ተመልሰው በአርባምንጭ የመጀመርያ 11 ተካተዋል፡፡ ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተደረገው ጨዋታ የተጎዳው አንተነህ መሳ በመሳይ አያኖ ተተክቷል፡፡

*በዳሽን ቢራ በኩል ዮናስ ግርማይ ወደ መጀመርያ 11 ሲመለስ አምሳሉ ጥላሁን ባልተለመደ ሁኔታ የመስመር አጥቂ ሆኖ ይጫወታል፡፡

የዳሽን ቢራ አሰላለፍ

ደረጄ አለሙ

ዮናስ ግርማይ – መላኩ ፈጠነ (አምበል) – ያሬድ ባየህ – ሱሌማን ካማራ

አስራት መገርሳ – ደረጄ መንግስቱ – ምንያህል ይመር
አምሳሉ ጥላሁን – ኤዶም ሆውሶሮቪ – ተክሉ ተስፋዬ

********//*********

የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ

መሳይ አያኖ

ፀጋዬ አበበ – በረከት ቦጋለ (አምበል) – አበበ ጥላሁን – ወርቅይታደል አበበ

ትርታዬ ደመቀ – አማኑኤል ጎበና – በረከት ደሙ – ታደለ መንገሻ

በረከት ወ/ፃድቅ – ተሾመ ታደሰ width=

ያጋሩ