ወላይታ ድቻ የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾቹን ውል ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል

ወላይታ ድቻ የተከላካዩ ደጉ ደበበ እና አማካዩ ተስፋዬ አለባቸውን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ሊያራዝም ከስምምነት ደርሷል፡፡

በአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ እየተመራ ስኬታማ የድል ሳምንታትን እያሳለፈ የሚገኘው ወላይታ ድቻ ለሁለተኛው ዙር የውድድር ወቅት ክለቡ ራሱን ለማጠናከር ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት አዳዲስ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርም ይጠበቃል፡፡ ክለቡ አዳዲስ ተጫዋቾች ከማስፈረም ባሻገር በክለቡ ውስጥ ውላቸው የተጠናቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾችን ውል ማራዘሙን ቀዳሚ ተግባሩ አድርጓል፡፡በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በዚህ ወቅት ወላይታ ድቻን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅለው የነበሩት አንፋዎቹ የተከላካይ አማካዩ ተስፋዬ አለባቸው እና ከመሐል ተከላካዩ ደጉ ደበበ በክለቡ ለቀጣዩ አንድ ዓመት በጦና ንቦቹ ቤት ለመቆየት ከስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን መስኮቱ ሲከፈትም ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ