የጅማ ከተማ አስተዳደር የክለቡን አንገብጋቢ ችግር ለመፍታት ከሌላ የሥራ ሴክተር ገንዘብ በማዞር ለተጫዋቾቹ ለጊዜውም ቢሆን የሁለት ወር ደሞዝ ክፍያ ፈፅሟል።
በተደጋጋሚ በሚነሳበት የተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ ጥያቄ ምክንያት ቡድኑ ከሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ይልቅ ትኩረቱን አስተዳደራዊ ችግር መፍታት ላይ ሲባዝን የቆየው የ2010 የሊጉ ቻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር ከ14ኛ ሳምንት ጨዋታ ማግስት ልምምድ አቋርጠው መቆየታቸውን መግለፃችን ይታወቃል።
ትናንት ማምሻውን የከተማው አስተዳደር ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ከሌላ የሥራ ሴክተር ላይ ገንዘብ በማዞር ለተጫዋቾቹ ለጊዜውም ቢሆን የሁለት ወር ደሞዝ ክፍያ ፈፅሟል። ዛሬ ረፋድ አዲስ አበባ የሚገባው ቡድኑ ነገ ሀዲያ ሆሳዕናን ወደሚገጥምበት ከተማ ሀዋሳ የሚያመራ ይሆናል።
©ሶከር ኢትዮጵያ