ድሬዳዋ ከተማ ከናይጄሪያዊው አጥቂ ጋር ተለያየ

በክረምቱ ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሎ የነበረው ናይጄሪያዊው አጥቂ ፕሪንስ ባጅዋ አዴሴጎን ከድሬዳዋ ጋር መለያየቱን ክለቡ አስታውቋል፡፡

ለድሬዳዋ ከተማ ለአንድ ዓመት ለመጫወት የተቀላቀለው አጥቂው በክለቡ የቋሚነት ቦታን ለማግኘት ሲቸገር የተስተዋለ ሲሆን ከአንድ ጨዋታ በቀር በመጀመርያ ተሰላፊነት ሳይጫወት ቀርቷል፡፡ በተደጋጋሚ አቋሙን እንዲያስተካክል ማስጠንቀቂያ የደረሰው የቀድሞው የኢኑጉ ሬንጀርስ እና ሰንሻይን ስታርስ ተጫዋች አቋሙን ማስተካከል ባለመቻሉ ከክለቡ ጋር ዛሬ ተለያይቷል፡፡

በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾች በዝውውር እና በውሰት ለማስፈረም በዝግጅት ላይ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ከመቐለ 70 እንደርታ እንዳለ ከበደን ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱ ይታወቃል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ