ዮናስ በርታ ከአዳማ ከተማ ጋር ተለያይቷል

በክረምቱ አዳማ ከተማን ተቀላቅሎ የነበረው ዮናስ በርታ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

ከዚህ ቀደም በባህር ዳር ከተማ የተጫወተውና ዐምና በደቡብ ፖሊስ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ዮናስ ዘንድሮ አዳማ ከተማን በመቀላቀል ጥሩ ጊዜ ያሳልፋል ተብሎ ቢጠበቅም አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ በአንድም ጨዋታ ላይ ሳይጠቀሙበት ቀርተው ዛሬ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ቀርቦለት የነበረው ዮናስ ምንም አይነት ጉዳት ባይኖርበትም ጥቂት ጨዋታዎች ላይ የ18 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ከመካተቱ በቀር ምንም ጨዋታ አለማድረጉ አስገራሚ ሆኗል።

ዮናስ ከቀናት በኋላ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ወደ አንድ የፕሪምየር ሊግ ቡድን ሊያመራ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ