ድሬዳዋ ከተማ ሁለት ጋናውያንን አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ተከላካዩ ክዌኩ አንዶህ እና አጥቂው ፉሴይኒ ኑሁን ማስፈረሙን አስታውቋል።

ጋናዊው የተከላካይ መስመር ተጫዋች ኩዌኩ አንዶህ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ለደደቢት በመፈረም ሲሆን ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ውሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ ከቡድኑ ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። በዓመቱ መጀመርያ ወደ ወልቂጤ ለማምራት የነበረ ቢሆንም ሳይስማማ በመቅረቱ ሳይፈርም መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ምስራቁ ክለብ አምርቷል። ዛሬ ከቡድኑ ጋር የተለያየው ዘሪሁን አሸሼቦን ቦታ ይሸፍናል ተብሎም ይጠበቃል

ሌላው ለድሬዳዋ የፈረመው ፉሴይኒ ኑሁ ነው። ጋናዊው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች በ2010 በመቐለ 70 እንደርታ ያሳለፈ ሲሆን ዓምና በዚህ ወቅት ለደደቢት ፈርሞ ለአንድ ዓመት ከተጫወተ በኋላ ከሳምንት በፊት ውሉን አጠናቆ በመለያየት ወደ ድሬዳዋ አምርቷል። በአጥቂ ስፍራ ናይጄርያዊው ባጅዋ አዴገሰንን የለቀቁት ድሬዎች ቦታውን በጋናዊው አጥቂ ተክተዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ