የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወልዋሎን አግዷል

ባለፈው ዓመት ወልዋሎን ካገለገሉት ስምንት ተጫዋቾች ጋር በተያያዘ በጥር 14 በፍትህ አካላት በአስር ቀናት ውስጥ ባለ ጊዜ ውሳኔውን እንዲተገብሩ የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው የነበሩት ወልዋሎዎች የፍትህ አካልን ውሳኔ በጊዜው ባለመፈፀማቸው ከማንኛውም ውድድር ታግደዋል።

ከደስታ ደሙ፣ ቢንያም ሲራጅ፣ ዳንኤል አድሐኖም፣ ኤፍሬም አሻሞ፣ ብርሀኑ አሻሞ፣ ብርሀኑ ቦጋለ፣ አማኑኤል ጎበና እና ሳምሶን ተካ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ስማቸው ሲነሳ የቆየው ወልዋሎዎች በመጨረሻም ከውድድሩ መታገዳቸውን ጉዳዩን ሲከታተሉ ከቆዩት ወኪል እና የህግ ባለሞያ አቶ ብርሀኑ በጋሻው አረጋግጠናል።

የዕግድ ደብዳቤ፡-

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ