ባምላክ ተሰማ ተጠባቂውን የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ይመራል

ኢትዮጵያዊው የመሐል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ቲፒ ማዜምቤ በሜዳው የሞሮኮው ራጃ ካዛብላንካን የሚያስተናግድበት የቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ እንዲመራ ተመርጧል።

የመጀመርያ ጨዋታው በመጪው ዓርብ ካሳቤላንካ ላይ የሚደረግ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ሉሙምባሺ ላይ ቅዳሜ መጋቢት 7 ይደረጋል። ይህን የመልስ ጨዋታ ነው ባምላክ ተሰማ እንዲመራ የተመደበው።

ከወራት በፊት የግብፁ ዛማሌክ እና የዛምቢያው ዜስኮ ጨዋታ ከረዳቶቹ ተመስገን ሳሙኤል እና ለሚ ንጉሴ ጋር በመሆን የመራው ባምላክ በዚህ ጨዋታ ረዳቶቹ ሆነው ጨዋታውን የሚመሩት ዳኞች እስካሁን ድረስ አልታወቁም።

ከወዲሁ በርካታ ተጠባቂ ጨዋታዎች ያሉት ይህ ውድድር በሩብ ፍፃሜው አል አህሊን ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ዋይዳድ ካዛብላንካን ከ ኤቷል ደ ሳህል፣ ዛማሌክን ከኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ እና ራጃ ካዛብላንካን ከ ቲፒ ማዜምቤ አገናኝቷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ