ወልዋሎ ከአራት ተጫዋቾች ጋር ተለያይቷል

ባለፈው ሳምንት ከኬኔዲ አሺያ ጋር የተለያዩት ቢጫ ለባሾቹ አሁን ደግሞ ከአራት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ተለያይተዋል።

ከክለቡ ጋር የተለያዩት ከኢትዮጵያ መድን ቡድኑን የተቀላቀሉት አማካዮቹ ዘሪሁን ብርሀኑ እና ሚካኤል ለማ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ የፈረመው ብሩክ ሰሙ እና በመጨረሻው የዝውውር ቀናት አክሱም ከተማን ለቆ ቡድኑን የተቀላቀለው ኤርምያስ በለጠ ናቸው።

በአጋማሹ የዝውውር መስኮት በስፋት ይሳተፋሉ ተብለው የሚጠበቁት ወልዋሎዎች በቀጣይ ቀናትም ከሌሎች ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ይለያያሉ ተብሎ ሲጠበቅ በቅርብ ቀናትም አዲስ አሰልጣኝ ይቀጥራሉ ተብሎ ይገመታል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ