አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ

የስሑል ሽረው አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ታውቋል።

ባለፈው ዓመት አጋማሽ ስሑል ሽረን ተቀላቅለው ቡድኑ በፕሪምየር ሊጉ እንዲቆይ ያስቻሉት አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ለክለቡ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ከቡድኑ ጋር ከመጥፎ አጀማመር አገግመው ቡድኑ በተከታይ ጨዋታዎች ሽንፈት ሳያስተናግድ ደረጃውን እንዲያሻሽል ያደረጉት አሰልጣኙ መልቀቂያው ከሰዓታት በፊት ለክለቡ መስጠታቸውን ከማወቅ ተችሏል።

በቀጣይ የክለቡ ምላሽ እና ተያያዥ ጉዳዮችን እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ