ኢትዮጵያ ቡና 1-2 ሲዳማ ቡና
47′ አማኑኤል ዮሃንስ
: 38′ አዲስ ግደይ
, 62′ ፍፁም ተፈሪ
—————
ተጠናቀቀ !!!!
ሲዳማ ቡና ባለሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን 2-1 አሸንፏል፡፡
90′ የተጫዋች ቅያሪ – ሲዳማ ቡና
ተከላካዩ እምሻው ካሱ አማካዩ አዲስ ግደይን ቀይሮ ገብቷል፡፡ አዲስ ከቡና ደጋፊ ጭብጨባ ተለግሶታል፡፡
90′ አራተኛ ዳኛው ተጨማሪ 4 ደቂቃ ጨምረዋል፡፡
88′ ከመአዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ፓትሪክ ሞክሮ በለአለም በቀላሉ ተይዞበታል፡፡
87′ ቡና ወደ ሲዳማ የግብ ክልል ይበልጥ ተጠግቶ ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ለአለም ብርሃኑን የሚፈትን ጥቃት መፈፀም አልቻሉም፡፡
84′ ሳውረል ኦልሪሽ ከረጅም ርቀት በቀጥታ የመታውን ቅጣት ምት ወንድወሰን አድኖታል፡፡
82′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
ዮሴፍ ዳሙዬ በአማኑኤል ዮሃንስ ተቀይሮ ገብቷል፡፡
79′ አዲስ ግደይ ያጠፈለትን ኳስ ተጠቅሞ ፍፁም ተፈሪ ወደ ግብ ቢሞክርም ወንድወሰን በቀላሉ ይዞበታል፡፡
79′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
ኤሪክ ሙራንዳ እና ወሰኑ ማዜ ወጥተው አንዱአለም ንጉሴ እና ተመስገን ካስትሮ ገብተዋል፡፡
77′ ወንድይፍራው ጌታሁን በወሰኑ ማዜ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመዞበታል፡፡
76′ ኢትዮጵያ ቡና የአቻነት ጎል ፍለጋ ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ሳዲቅ ሴቾ ጥሩ የግብ ማግባት እድል ቢያገኝም ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
73′ ኤሪክ ሙራንዳ የሞከረው ኳስ በተከላካዮች ተጨርፎ የማዕዘን ምት ሆኗል፡፡ ከማዕዘን የተመለሰውን ኳስ ወሰኑ ማዜ ከርቀት መትቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
72′ ጥላሁን ከቀኝ መስመር ያሻማው ኳስ የግቡን ቋሚ ገጭቶበታል፡፡
*አዲሱ ፈራሚ ፓትሪክ ቤናውን ለኢትዮጵያ ቡና የመጀመርያ ጨዋታውን እያደረገ ይገኛል፡፡
64′ የተጫዋች ቅያሪ – ኢትዮጵያ ቡና
-ኤልያስ ወጥቶ ፓትሪክ ገብቷል፡፡ ሳዲቅ ሴቾ እያሱን ተክቶ ወደ ሜዳ ገብቷል፡፡
62′ ጎልልልል ፍፁም ተፈሪ
ፍፁም ተፈሪ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ሲዳማን በድጋሚ መሪ አድርጓል፡፡ ጎሏ ስታድየሙ ዝምታ እንዲሰፍንበት አድርጋለች፡፡
59′ ጨዋታው በሲዳማ የሜዳ ክፍል እየተደረገ ነው፡፡
*ሲዳማ ቡና የኤሪክ ሙራንዳን የአካል ብቃት እና አዲስ ግደይን ፍጥነት በመጠቀም በረጃጅም ኳሶች የቡና የግብ ክልል ለመድረስ እየጣሩ ነው፡፡
55′ ቡና በደጋፊዎቹ ህብረ ዜማ ታጅቦ ተጨማሪ ጎል ፍለጋ ወደ ፊት እየገፋ ነው፡፡
47′ ጎልልልል አማኑኤል ዮሃንስ
ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ አማኑኤል ቡናን አቻ አድርጓል፡፡
46’ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡
———————
ተጠናቀቀ!!!
የመጀመርያው አጋማሽ በሲዳማ መሪነት ተጠናቀቀ
45+2 ኤልያስ ማሞ ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
45+1′ ወሰኑ ማዜ በግምት ከ25 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ወደ ላይ ወጥቷል፡፡
45′ የጨዋታው 4ኛ ዳኛ 3 ተጨማሪ ሰአት አሳይተዋል
አዲስ ግደይ የቡና ተከላካዮችንበፍጥነት እና ክህሎት እየፈተነ ይገኛል፡፡ ጥላሁን ወልዴ ቢጫ ካርድ እንዲመዝበትም ምክንያት ሆኗል፡፡
ጎልልል አዲስ ግደይ
አዲስ ግደይ ከፍፁም ቅጣት ምት የቀኝ ጠርዝ አክርሮ የመታው ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አርፏል፡፡
35′ አዲስ ግደይ በረጅሙ የተላከለትን ኳስ ተቆጣጥሮ ተከላካዮችን በፍጥነት በማለፍ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
32′ ከቀኝ መስመር የተሻማውን ቅጣት ምት ኢኮ ፊቨር ወደ ውጪ አውጥቶታል፡፡ የተሰጠውን የማዕዘን ምት ወሰኑ ማዜ መትቶ ወንድወሰን ይዞታል፡፡
26′ የቡና ተጫዋቾች ወደ ሲዳማ የግብ ክልል ቢጠጉም ለአለምን መፈተሽ አልቻሉም፡፡
23′ ያቤውን ዊልያም እጅግ ለጎል የቀረበ ሙከራ አድርጎ የግቡን ቋሚ ታክኮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
18′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና የበላይነት ቀጥሏል፡፡ ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ እየደረሱም ይገኛሉ፡፡
17′ ኤልያስ ማሞ የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ላይ ወጥቷል፡፡
16′ ኢትዮጵያ ቡናዎች በ6ኛው ፣ 9ኛው ፣ 11ኛው ደቂቃዎች ጥሩ የግብ ማግባት ሙከራዎች አድርገዋል፡፡
1′ ጨዋታው ተጀመረ
* ኢትዮጵያ ቡና ከግራ ወደ ቀኝ ፣ ሲዳማ ቡና ከቀኝ ወደ ግራ ያጠቃሉ፡፡
————*———–
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
ወንድወሰን ገረመው
ጥላሁን ወልዴ – ወንድይፍራው ጌታሁን ኢኮ ፊቨር – ሳለአምላክ ተገኝ
ኤርሚያሰ በለጠ – አብዱልከሪም መሃመድ
እያሱ ታምሩ – ኤልያስ ማሞ(አምበል) – አማኑኤል ዮሃንስ
ያቤውን ዊልያም
——-//——–
የሲዳማ ቡና አሰላለፍ
ለአለም ብርሃኑ (አምበል)
ዘነበ ከበደ – አንተነህ ተስፋዬ – አወል አብደላ – ሳውሬል ኦልሪሽ
አዲስ ግደይ – ሙሉአለም መስፍን – አሳምነው አንጀሎ – ፍፁም ተፈሪ – ወሰኑ ማዜ
ኤሪክ ሙራንዳ