ለፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች የሚሰጠው ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ ባየር ሙኒክ ጋር በመተባበር ለሴት እና ለወንድ ለፕሪምየር ሊግ አሰልጣኞች የሚሰጠው ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል።

አብዛኛዎቹ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች አሰልጣኞች የተካፈሉበት ይህ ስልጠና ዛሬ ረፋድ ላይ ነበር በአዲስ አበባ ስታዲየም መሰጠት የጀመረው። ከሁለት ቀናት በኋላ ይጠናቀቃል በተባለው በዚህ ስልጠና አምስት መሠረታዊ ነጥቦች ላይ ያተኩራል። እነርሱም የባየር ሙኒክ የሚከተው የጨዋታ ፍልስፍና፣ የታክቲክ አቀራረብ፣ የአሰልጣኝ ስብዕና እና ጨዋታ የመረዳት አቅም፣ ጨዋታ ላይ የሚያጋጥሙ የውሳኔ አሰጣጥ ዙርያ እና አራቱ የቅድመ ዝግጅት ወቅቶች አሰልጣኞች ሊከተሉት የሚገቡ ነገሮች የስልጠናው አካል ናቸው።

ጠቃሚ ዕውቀት ይገኝበታል ተብሎ የታመነበት ስልጠና ጠዋት በንድፈ ሀሳብ ከሰዓት በተግባር ላይ በማተኮር ቀጥሎ ረቡዕ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ