አንጋፋው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ መካከል የነበረው ክስ ዙርያ ፌዴሬሽኑ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
ከታዳጊ ቡድን አንስቶ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ያገለገለው እና ያለፉትን ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስኬታማ ቆይታ በማድረግ በኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ እና አዳማ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው ታፈሰ ተስፋዬ ዳግም በ2010 ወደ አሳዳጊው የቀድሞ ክለቡ ተመልሶ መጫወቱ ይታወቃል። ሆኖም ኮንትራቱ ጥር 30 ቀን 2012 የሚያበቃ ቢሆንም ቀሪ የስድስት ወር ኮንትራት እየቀረው ያለ ተጫዋቹ ፍቃድ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነሐሴ 30 ቀን 2011 ውሉ እንዲቋረጥ ማድረጉን በመግለፅ ተጫዋቹ ክስ መስርቷል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ክስ መስርቶ ጉዳዩን ሲከታለተል የቆየው ታፈሰ በፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ አግኝቷል። በውሳኔው መሠረት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ክለብ ከነሐሴ 30 ቀን 2011 እስከ ጥር 30 ውሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ያልተከፈለው ወርኃዊ ደሞዝ ተሰልቶ እንዲከፈለው ወስኖለታል።
የውሳኔው ደብዳቤ
© ሶከር ኢትዮጵያ