ወላይታ ድቻ አቤቱታውን ለፌዴሬሽኑ ገለፀ

በአስራ አምስተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወላይታ ድቻን አስተናግዶ ባሸነፈበት ጨዋታ በነበረው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል የተነሳ ተበድያለሁ እና ፌዴሬሽኑ መልስ ይስጠኝ ሲል በደብዳቤ ጠየቀ፡፡

በጨዋታው የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እና በደጋፊዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት በተወሰኑ ደጋፊዎች ላይ ጉዳትን ማስተናገዱ አይዘነጋም። የወላይታ ድቻ ክለብም በጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና በኩል በደል ደርሶብናል ፌድሬሽኑም የደረሰብንን ተመልክቶ መልስ ይስጠን ሲል በላከው ደብዳቤ ገልጿል፡፡

ፎቶ – © Wolaitta Dicha


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ