የፕሪምየር ሊጉ አንደኛ ዙር ስብሰባ በሳምንቱ መጨረሻ ይደረጋል

ትናንት የተጠናቀቀው የአንደኛው የውድድር ዘመን አጋማሽ ሪፖርት እና ግምገማ በሳምንቱ መጨረሻ ይካሄዳል።

አዲስ በተዋቀረው ዐቢይ ኮሚቴ ሥር የተከናወነው የዘንድሮው ሊግ አጋማሹ ላይ እንደመድረሱ በየዓመቱ የተለመደው ስብሰባ በመጪው ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2012 በጁፒተር ሆቴል የሚከናወን ሲሆን የግማሽ ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የሊጉ ሁለተኛ የውድድር ዘመን አጋማሽ ከሁለት ሳምንታት ዕረፍት በኋላ በመጪው የካቲት 29 እና 30 እንዲጀምር መወሰኑን ትናንት መዘገባችን ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ