የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወሩ ምርጦች (ከጥር 24 – የካቲት 16)

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ የውድድር ዘመን አጋማሽ በዚህ ሳምንት መጀመርያ መጠናቀቁ ይታወቃል። ሶከር ኢትዮጵያም ከውድድር ዓመቱ ጅማሮ አንስቶ በየወሩ ጠቅለል ያሉ ቁጥራዊ መረጃዎች እና የወሩ ምርጦችን ስታቀርብ የቆየች ሲሆን በ3ኛው ወር መሰናዷችንም እንደተለመደው ከጥር 24 ወዲህ በተደረጉ አራት ሳምንታት የተደረጉ ጨዋታዎችን ተመርኩዘን የወሩን ምርጦች አዘጋጅተናል።
አጠቃላይ የወሩ መረጃ
የጨዋታ ብዛት – 32 (እያንዳንዱ ቡድን 4 ጨዋታ)
የተቆጠሩ ጎሎች ብዛት – 83
በአማካይ በጨዋታ – 2.3
የማስጠንቀቂያ (ቢጫ) ካርድ ብዛት – 119
የቀይ ካርድ ብዛት – 8


ከፍተኛ ነጥብ የሰበሰቡ ቡድኖች
1. ወላይታ ድቻ – 9 ነጥብ / +3 ጎል
2. ሲዳማ ቡና – 9 ነጥብ / -1 ጎል
3. ቅዱስ ጊዮርጊስ – 8 ነጥብ / +7 ጎል


ዝቅተኛ ነጥብ የሰበሰቡ ቡድኖች
1. ወልዋሎ ዓዩ – 1 ነጥብ / -6 ጎል
2. መቐለ 70 እንደርታ – 3 ነጥብ / +0 ጎል
3. ድሬዳዋ ከተማ – 4 ነጥብ / -3 ጎል


የጎሎች መረጃ
አጠቃላይ ጎል – 83
በጨዋታ የተቆጠሩ – 74
በፍ/ቅ/ም የተቆጠሩ – 9
በራስ ላይ የተቆጠሩ – 2
የመከኑ ፍ/ቅ/ምቶች – 1
ጎል ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ብዛት – 54
በርካታ ጎል ያስቆጠረ ቡድን – ቅዱስ ጊዮርጊስ (12)
ከፍተኛ ጎል የተቆጠረበት ቡድን – ወልዋሎ (10)
ዝቅተኛ ጎል ያስቆጠረ ቡድን – ሀዲያ ሆሳዕና (2)
ዝቅተኛ ጎል የተቆጠረበት ቡድን – ስሑል ሽረ (2)

በዚህ ወር አቤል ያለው በጎል አስቆጣሪነቱ የመጀመርያው ረድፍ ላይ ተቀምጧል።


አሲስት

ለጎል አመቻችቶ በማቀበል ረገድ ሚኪያስ መኮንን ጥሩ ወር አሳልፏል። በወሩ በተደረጉ አራት ጨዋታዎች ሦስት ኳሶችን በማመቻቸት ቀዳሚ ነው።

በዚህ ወር በአጠቃላይ 47 ተጫዋቾች ለጎል በማመቻቸቱ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን ሁለት እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡትን በዚህ መልኩ ተመልክተናቸዋል።


የጎል ተሳትፎ

ጎሎች በማስቆጠር አልያም በማመቻቸት ብዙ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገው የቅዱስ ጊዮርጊሱ አቤል ያለው ነው። አቤል አምስት ጎሎች አስቆጥሮ ሁለት ኳሶች በማመቻቸት በአጠቃላይ በ7 ጎሎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል። በአጠቃላይ በተሳትፎ ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገቡ የወሩ ምርጦች እነዚህን ይመስላሉ፡-


ግብ ጠባቂዎች

በዚህ ወር የወላይታ ድቻው ግብ ጠባቂ መክብብ ደገፉ ከአራት ጨዋታዎች በሦስቱ ጎሉን ሳያስደፍር ቀዳሚ መሆን ችሏል። አዳማ ከተማ እንደ ድቻ ሁሉ በተመሳሳይ ሦስት ጨዋታ መረቡን ባያስደፍርም ሁለቱን ጃኮ ፔንዜ አንዱን ደረጄ ዓለሙ በመሰለፋቸው መክብብ ቀዳሚ ሊሆን ችሏል። የዚህ ወር ደረጃ ይህንን ይመስላል፡-


የወሩ ምርጥ ተጫዋች
አቤል ያለው – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ፈጣኑ የመስመር አጥቂ በዚህ ወር ምርጥ እንቅስቃሴ ማሳየት ችሏል። ተጫዋቹ ሲዳማ ቡናን 6-2 ባሸነፉበት ጨዋታ እጅግ የተዋጣለት እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ከፋሲል ከነማ እና ወልዋሎ ጋር በተደረጉት ጨዋታዎችም እንቅስቃሴው ግሩም ነበር። በወሩ ከተደረጉ አራት የሶከር ኢትዮጵያ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን ምርጫዎች በሦስቱ ላይ የተካተተው አቤል በወሩ 5 ጎሎች አስቆጥሮ 2 ኳሶችን ደግሞ በማመቻቸትም በቁጥራዊ መረጃ ልቆ ተገኝቷል።
ሌሎች የወሩ ምርጥ ተጫዋቾች

2. ጫላ ተሺታ (ወልቂጤ ከተማ)

3. ጌታነህ ከበደ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)የወሩ ውጤታማ አሰልጣኝ
ደለለኝ ደቻሳ (ወላይታ ድቻ)

በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ወሩን ያሳለፈው ወጣቱ አሰልጣኝ ወላይታ ድቻን ወደ ጥሩ ጎዳና መምራት ችሏል። ቡድኑ በወሩ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ሦስቱን ያሸነፈ ሲሆን በተለይ በሜዳቸው ድሬዳዋ ከተማን የረቱበት ጨዋታ ድንቅ አቋማቸው የታየበት ነበር። በተጨማሪም ቡድኑ በ3 ተከታታይ ጨዋታዎች ጎሎች አለማስተናገዱ በአሰልጣኙ ሥር የተረጋጋ ወር ማሳለፉን የሚያመለክቱ ናቸው።
ሌሎች የወሩ ምርጦች

2. ሰርዳን ዝቪጅኖቭ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

3. ዘርዓይ ሙሉ (ሲዳማ ቡና)


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ