ፕሪምየር ሊጉ ከዐቢይ ኮሚቴነት ወደ ኩባንያነት ተለውጧል

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ዐቢይ ኮሚቴ ህጋዊ የኩባንያ ዕውቅና አግኝቶ “የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካምፓኒ” ወደሚለው ስያሜ ተቀይሯል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በጁፒተር ሆቴሌ የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር የውድድር ዘመን አጋማሽ ግምገማ እየተካሄደ ሲሆን በዛሬው ጉባዔ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ በመክፈቻ ንግግር አስጀምረዋል። ሰብሳቢው በመክፈቻ ንግግራቸው በአንደኛው ዙር ክለቦች ራሳቸው ባቋቋሙት የሊግ ዐቢይ ኮሚቴ እየተመራ ሲሆን ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዐቢይ ኮሚቴ የሚለው በክለቦች ውይይት መሠረት ወደ ኩባንባነት በመሸጋገሩ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሊግ ካምፓኒ ወደሚል ስያሜ መለወጡን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ደግሞ የካምፓኒውን መመስረት የሚያረጋግጥ የዕውቅና ሰርተፍኬት መረከባቸውንም በንግግራቸው እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለታዳሚው ገልፀዋል፡፡

የስብሰባው አዳዲስ ጉዳዮች እየተከታተልን እንገልፃለን

© ሶከር ኢትዮጵያ