ዛሬ በጁፒተር ሆቴል እየተደረገ ባለው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር ግምገማ ላይ የወልቂጤ ሜዳ እየተነሳበት ባለው ቅሬታ መነሾነት በድጋሚ ጠንካራ ግምገማ ሊደረግበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመን መስከረም 28 ሲጀምር ከውድድሩ ቀደም ብሎ ሜዳቸው መሻሻል አለባቸው በሚል ከተጠቀሱት ሜዳዎች መካከል አንዱ የወልቂጤ ስታዲየም ነበር፡፡ ክለቡ የመጀመርያ ሦስት ጨዋታዎችን ሜዳው ዕድሳት ያስፈልገዋል በመባሉ ከሜዳው ውጪ ለመጫወት የተገደደ ሲሆን ሜዳው ከተጠናቀቀ በኋላ ግን ወደ ሜዳው ተመልሶ በርካታ ጨዋታዎችን እያደረገ አንደኛውን ዙር አጠናቋል፡፡ በዛሬው የሊጉ ግምገማ ከኮሚሽነሮች እና ከተለያዩ አካላት ሜዳው መሻሻል አለበት በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታዎች እየተነሱበት በመሆኑ ለሁለተኛው ዙር ሜዳው መስተካከል ስላለበት ጠንካራ ግምገማ ይደረግበታል ሲሉ የሊግ ካምፓኒው ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ