ለፕሪምየር ሊጉ አዲስ መለያ (ሎጎ) መፅደቁ ተገለፀ

ከዚህ ቀደም ምንም አይነት ይፋዊ አርማ ያልነበረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሁን አዲስ መለያ አግኝቷል።

ዐቢይ ኮሚቴው አርማውን ለማሰራት ጨረታ ያወጣ ሲሆን በርካታ አካላትም መወዳደር ችለዋል። ኮሚቴው ከቀረቡት በርካታ አማራጮችም አንዱን እንደመረጠ ያሳወቀ ሲሆን አርማው ይፋ ከመደረጉ በፊት ለአሸናፊው አካል የሚከፈለውን ክፍያ ለመፈፀም የሊጉ ዐብይ ኮሚቴ ወደ ሊግ ኩባንያነት የሚያደርገው ሽግግር እየተጠበቀ እንደሆነ እና ቅድመ ሁኔታዎቹ ሲሟሉም አርማው ለዕይታ ይፋ እንደሚሆን ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወጥ የሆነ እና በየውድድር ዓመቱ የማይቀያየር ዋንጫ እንዲኖረው የዋንጫ ዲዛይን ለማሰራት ኮሜቴው በቅርቡ አዲስ ጨረታ እንደሚያወጣ ያስታወቀ ሲሆን በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ዲዛይነሮችም በጨረታው እንዲሳተፉበት የፕሪምየር ሊጉ ኩባንያ ሊቀ መንበር መቶ አለቀ ፈቃደ ማሞ ጠይቀዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ