ኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቷል

የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ዲፓርትመት እያዘጋጀው ባለው ስልጠና አስመልክቶ እየቀረቡ ባሉ አቤቱታዎች ዙርያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቷል።

ምስረታውን ካደረገበት ወቅት ጀምሮ ለተጫዋቾች እና አሰልጣኞች መብት ከመታገል በተጓዳኝ የተለያዩ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎች ከፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር እያዘጋጀ የሚገኘው ማኅበሩ የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዲፓርትመት በተለያዩ ጊዜያት ተዘጋጅተው እየቀረቡ ባሉ ስልጠናዎች ዙርያ አባላቶቼ ቅሬታዎችን እያቀረቡ ነው በማለት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቷል።

ማክሰኞ የካቲት 24 ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በተጠራው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዝርዝር ሀሳቦች ይቀርቡበታል ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ