ወላይታ ድቻ የመጀመሪያ ተጫዋቹን ሲያስፈርም የደጉ ደበበን ውልም አራዝሟል

የጦና ንቦቹ የግራ መስመር ተከላካዩ አበባው ቡጣቆን ሲያስፈርሙ የደጉ ደበበን ውል አራዘሙ፡፡

አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳን ከጊዜያዊ ወደ ዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ወላይታ ድቻ ከሰሞኑ ከአራት ተጫዋቾችን ጋር በስምምነት የሚለያይ ሲሆን በምትኩ ደግሞ ከአሁን አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ላይ ሲሆን የመጀመሪያ ተጫዋቹንም በእጁ አስገብቷል፡፡ የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አበባው ቡታቆ በ2011 የውድድር ዘመን ቢጫ ለባሾቹ ደቡብ ፓሊሶችን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሎ በመጫወት በክለቡ ያሳለፈ ሲሆን ዘንድሮ በአንደኛው ዙር የፕሪምየር ሊግ ጉዞ ካለ ክለብ ከቆየ በኋላ ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ እስከ ዓመቱ መጨረሻ በወላይታ ድቻ ለመጫወት ዛሬ አመሻሽ ለክለቡ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ባለፈው ዓመት በዚህ የዝውውር ወቅት ፈረሰኞችን ለቆ ወላይታ ድቻን የተቀላቀለው እና ውሉ በመጠናቀቁ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና ያመራል ሲባል የነበረው የመሐል ተከላካዩ ደጉ ደበበ በክለቡ ውሉን ማራዘሙ ተገልጿል።

© ሶከር ኢትዮጵያ