ቶጓዊው አጥቂ ከሰበታ ከተማ ጋር ልምምድ ጀምሯል

ከሳምንታት በፊት ከወልቂጤ ከተማ ጋር የተለያየው ቶጓዊው አጥቂ ከሰበታ ከተማ ጋር ልምምድ ጀምሯል።

አጥቂው በክረምቱ የዝውውር መስኮት ባህር ዳር ከተማን ለቆ ወደ ወልቂጤ ከተማ ካመራ በኃላ የሰራተኞቹ የዓመቱ የመጀመርያ ግብ ቢያስቆጥርም የቡድኑ ቆይታ ብዙም ሳይዘልቅ ከሳምንታት በፊት በስምምነት መለያየቱ ይታወሳል። በኢትዮጵያ ቆይታው ለሀዋሳ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ባህርዳር ከተማ እና ለወልቂጤ ከተማ መጫወት የቻለው ይህ አጥቂ አሁን ከቡድኑ ጋር ልምምድ በመስራት ላይ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ወደ ሰበታ ከተማ የሚያደርገው ዝውውር ሙሉ ሙሉ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። በቡድኑም ጥሩ አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል።

ሰበታ ከተማዎች ከጃኮ አረፋት በተጨማሪ በኢትዮ- ኤሌክትሪክ ጥሩ ቆይታ የነበረው ፒተር ንዋድኬን ዝውውር ለማጠናቀቅ በጥረት ላይ እንዳሉ ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ