አክሊሉ አየነው ከወልዋሎ ጋር ልምምድ ጀምሯል

የመሐል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ አክሊሉ አየነው ዛሬ ከወልዋሎ ጋር ልምምድ ጀምሯል።

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ በሙገር ሲሚንቶ፣ ደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና የተጫወተው ይህ ተጫዋች ከኢትዮጵያ ውጭም ለየመኑ አልሳቅር የተጫወተ ሲሆን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ከተለያየ በኋላ ዘንድሮ ያለ ክለብ ቆይቷል።

ከመሐል ተከላካይነት በተጨማሪ በአማካይ ቦታም መጫወት የሚችለው አክሊሉ በቀጣይ ቀናት ከወልዋሎ ጋር የሚያቆየውን ውል ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ ቡድኑን ከተቀላቀለም በደደቢት ተጣማሪው ከነበረው ዓይናለም ኃይለ ጋር በድጋሚ ይገናኛል። በተጨማሪም በጉዳት እየታመሰ ለሚገኘው የቡድኑ ተከላካይ መስመር ጥሩ አማራጭ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን አዲስ አሰልጣኝ አድርገው የቀጠሩት ወልዋሎዎች በቀጣይ ቀናት በርካታ ተጫዋቾች ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ