ባለፈው ሳምንት ከጅማ አባ ጅፋር ጋር የተለያየው ብሩክ ገብረአብ ወደ ወልዋሎ ለመመለስ ተስማማ።
ስሑል ሽረን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ከረዳ በኋላ ወደ ጅማ አባ ጅፋር አምርቶ ከቡድኑ ጋር የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ቆይታ ያደረገው ይህ አማካይ ከዓመታት በኋላ ወደ እናት ክለቡ ወልዋሎ ተመልሷል።
በዚህ የውድድር ዓመት ለጅማ አባጅፋር ስምንት ጨዋታዎች ያደረገው ብሩክ በተሰለፈባቸው 429 ደቂቃዎች አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል። የእግር ኳስ ህይወቱን ወልዋሎን ወደ ከፍተኛ ሊግ በማሳደግ ሀ ብሎ የጀመረው ብሩክ ገብረአብ በነገው ዕለት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ለመጀመር ዓዲግራት ከተማ ገብቷል።
በቀጣይ ቀናትም በርካታ ዝውውሮች ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት ወልዋሎዎች ሁለት አማካዮችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ