ኤልያስ ማሞ በድሬዳዋ ውሉን አራዘመ

ከቀናት በፊት ኮንትራቱ ተጠናቆ የነበረው ኤልያስ ማሞ ከክለቡ ጋር ያለውን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሷል።

የአማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ባለፈው የውድድር ዓመት በዚህ ወቅት ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሎ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን ከቡድኑ ጋር ለሁለተኛው ዙር ዝግጅት አለመጀመሩን ተከትሎ ከክለቡ ጋር የመቀጠሉን ሁኔታ አጠራጣሪ ከመሆን ባለፈ ከተለያዩ ክለቦች ጋርም ስሙ ሲነሳ ቆይቷል። ሆኖም ከብርቱካናማዎቹ ጋር ለቀጣዩ አንድ ዓመት ተጨማሪ ጊዜን ለመቆየት ፊርማውን ፌዴሬሽን በመገኘት አኑሯል።

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ጅማ አባ ጅፋር እና ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አማካይ ዘንድሮ በድሬዳዋ በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ