ሄኖክ ኢሳይያስ በይፋ ለድሬዳዋ ከተማ ፈረመ

አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የተጠመደው ድሬዳዋ ከተማ አራተኛ አዲስ ተጫዋች በማድረግ ከቀናት በፊት ስምምነት ፈፅሞ የነበረውን ሄኖክ ኢሳይያስን በይፋ አስፈርሟል፡፡

በዋናነት በአማካይ እና ግራ መስመር ተከላካይ ሥፍራ የሚጫወተው ሁለገቡ ሄኖክ ከዚህ ቀደም ከደደቢት፣ ጅማ አባ ጅፋር እና ዓምና ደግሞ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን ዓምና በዚህ ወቅት ወላይታ ድቻን በመልቀቅ ወደ መቐለ ካመራ በኋላ ከሳምንት በፊት ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ነበር ከመቐለ ጋር የተለያየው።

ሄኖክ በአንድ ዓመት ውል ወደ ብርቱካናማዎቹ ቤት ማምራቱን ተከትሎ በአማካይ እና የመስመር ተከላካይ ሥፍራዎች ላይ አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ