ወልቂጤ ከተማ የ17ኛው ሳምንት ጨዋታን የሚያደርግበት ሜዳ ታውቋል

በዲስፕሊን ኮሚቴ የሁለት የሜዳው ጨዋታዎች ቅጣት የተላለፈበት ወልቂጤ ከተማ ቅጣቱን ተግባራዊ የሚያደርግበት ሜዳ ተለይቶ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ14ኛው ሳምንት ወልቂጤ ላይ ወልቂጤ ከ ሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ በስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ምክንያት የሁለት ጨዋታ ቅጣት የተላለፈባቸው ወልቂጤዎች በተከታታይ የሚያደርጓቸው የ17ኛ እና 20ኛ ሳምንት የሜዳ ጨዋታዎቻቸውን በገለልተኛ ሜዳ የሚከውኑ ሲሆን እነዚህን ጨዋታዎችም ከወልቂጤ 158 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው አዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል።

በውሳኔው መሠረት ወልቂጤ ከአዳማ ከተማ የሚደርገው የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ ሀሙስ መጋቢት 3 ቀን 2012 በአዲስ አበባ ስታዲየም 10:00 ላይ ሲከናወን ከወላይታ ድቻ ጋር የሚያደርገው የ20ኛ ጨዋታም ወደፊት በሚታወቅ ቀን በዚሁ ስታዲየም እንደሚደረግ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። በዚህም ወልቂጤ ከ16ኛው ሳምንት እስከ 20ኛ ሳምንት ካሉት አምስት ጨዋታዎች መካከል አራቱን (ከጊዮርጊስ፣ ከአዳማ፣ ከሰበታ እና ከወላይታ ድቻ) አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ያደርጋል ማለት ነው።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ