ፋሲል ከነማ የ16ኛው ሳምንት ጨዋታ የሚያደርግበት ሜዳ ታውቋል

በዲስፕሊን ኮሚቴ የአንድ ጨዋታ ቅጣት የተጣለበት ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጭ ጨዋታውን የሚከናውንበት ሜዳ ተለይቶ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ14ኛው ሳምንት ጎንደር ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ባደረገው ጨዋታ በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት የአንድ ጨዋታ ቅጣት የተላለፈበት ፋሲል ከነማ የሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታውን በዚህ ሳምንት በሜዳው የሚያከናውን በመሆኑ በየትኛው ስታዲየም ይጫወታል የሚለው ጉዳይ መነጋገርያ የነበረ ሲሆን ባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም እንዲያከናውን መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል።

በውሳኔው ምክንያት ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ የሚያደርጉት የ16ኛ ሳምንት ጨዋታ ከጎንደር 180 ኪ/ሜ ርቀት በሚገኘው ባህር ዳር ቅዳሜ 9:00 ላይ ይደረጋል። ሜዳውን የሚጠቀምበት ባህር ዳር ከተማ ደግሞ በተመሳሳይ በ16ኛ ሳምንት ጅማ አባ ጅፋርን እንደሚያስተናግድ ጨዋታን እሁድ እንደሚያከናውን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ