ድሬዳዋ ከተማ ሦስተኛ ተጫዋቹን አስፈረመ

ድሬዳዋ ከተማ ምንያምር ጴጥሮስን በአንድ ዓመት ውል አስፈረመ፡፡

ለሁለተኛው ዙር የውድድር ዘመን ራሱን አጠናክሮ ከነበረበት የውጤት ማጣት ችግር በቶሎ አገግሞ ወደ ተፎካካሪነት ለመመለስ ጥረት እያደረገ ያለው ድሬዳዋ ከተማ የቀኝ መስመር ተከላካይ ሥፍራ ተጫዋቹን ምንያምር ጴጥሮስን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡ ከ2007 ጀምሮ ያለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ቡድን ውስጥ ሲጫወት የቆየው ይህ ተጫዋች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ድሬዳዋ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሶ የነበረ ቢሆንም በተወሰኑ ጉዳዮች መስማማት ሳይችል በመቅረቱ በወቅቱ መፈረም አልቻለም ነበር፡፡ ሆኖም ከስድስት ወራት የከፍተኛ ሊግ የአዲስ አበባ ከተማ ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ብርቱካናማዎቹን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡ በቀኝ መስመር ተከላካይ ቦታ ላይ ለመሰለፍም ከወጣቱ ያሲን ጀማል ጋር ይፎካከራል።

ድሬዳዋ አስቀድሞ ጋናዊያኑ ኩዌኩ አንዶህ (ተከላካይ) እና ፉሴይኒ ኑሁ (አጥቂ) ማስፈረሙ ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ